Prosperity Party

ከቃል እስከ ባህል 

ከቃል እስከ ባህል 

"የጸና በቃሉ" 

በቃ እንጂ ለአካል መች መከነ ቃል 
      የሚታይና ሚሻገር   ሆኗል
     ከስጋና ደም ከራስ ተስማምቶ
     ቃል ባሕል ሆኗል በተግባር ታይቶ
   
የፀና በቃሉ (7)
በብሩህ እይታ ደቂቃን ተጠቅሞ
ዘወትር እየሰራ ለቃልኪዳን ቆሞ
ይኸው ተበሰረ አምስት ክረምት ጠባ
ሲያለብስ ለወገን የልማቱን ካባ (2)

ትናንት በወረሰው የዘመን አዙሪት
ሲፈተን የኖረ በቀን እና በሌት
ያልቆመ በችግር ጸንቶ በፈተና
ነገን አሻጋሪ ዛሬም ብልጽግና
 
   የፀና በቃሉ (2)

እልፎች ያለፉበት የችግር አረንቋ
መሻገር ጀመርን በመደመር ቋንቋ
በሌማት ትሩፋት ማዕድን አጋርቶ
ማየት አስችሎናል ከሰንኮፍ አውጥቶ

ሀገር እንደጸሀይ ደምቃ ያየንበት
ተስፋን ያሰነቀን የህዳሴው ሙሌት
ቀንዲል እየሆነ የኮሪደር ልማት
ትሩፋት ታየበት የህልማችን ጉልበት

ጎስቋላ መንደሮች ህይወት የገፋቸው
ዘመናት ተጉዘው ዘመን የረሳቸው
ተገፎ ግርዶሹ ካንገት አሉ ቀና
ጎጆውን ቀልሶ ዛሬ ብልጽግና

የኑሮ ምንዱባን ፍቅር  ያቆያቸው
ሲኖሩ በሀዘን ርሃብ ተጣብቷቸው
የተስፋ ብርሃን ተማሪ ምገባ
ከደጃፍ ተገኝቶ አበሰልን እምባ
የፀና በቃሉ (2)
ነገን እያሳየን የህልማችን ጉልበት
ሰርተን እያሰራን ተሰልፈን ከፊት 
ይቀየራል ታሪክ ያለንበት ዛሬ
በብልህ አመራር በህዝባችን ፍሬ

በታሪክ ማህደር በትውልድ ተጽፎ
እናያለን ነገን ፈተናችን አልፎ
ይወደስ በዘመን የዛሬው ጉዟችን
ተንዶ ተራራው ደርሰን ከህልማችን።

የፀና በቃሉ (8)

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party