ያለፉት ዘጠኝ ወራት ተግባራት እና ስኬቶቻቸው!
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት አምራችነትን በማበረታታት፣ ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ በማስገባት፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት፣ የሀገር ውስጥ ገቢን በማሰባሰብ፣ ወጪ ምርቶችን በብዛት በማምረት፣ ከአንድ ጊዜ በላይ መሬትን ደጋግሞ በማረስ፣ ሪፎርሞችን በየዘርፋቸው አግባብ በመተግበር፣ የተመዘገቡ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ የተነሣ ራስን የመቻል ተነሣሽነት ጨምሯል፡፡ ዘጠኝ ክልሎች ሰብአዊ ድጋፍን በራሳቸው ዐቅም ከመሸፈናቸውም በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥርም ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ86% ቀንሷል፡፡ ሂደቱ ተረጂነትን መጸየፍና አምራችነትን ባህል ማድረግ በሀገራችን ሥር እየያዘ መሆኑን አመላካች ነው፡፡