በሚዲያ፣ ኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዙሪያ ለጋምቤላ ክልል አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል
በሚዲያ፣ ኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዙሪያ ለጋምቤላ ክልል አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል
በብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት "የድህረ እውኘት ዘመንን በእውነትና በእውቀት" በሚል መሪ ቃል ለሚዲያ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬ ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል መሰጠት ጀምሯል።
በዚሁ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ የሚተገብራቸዉ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ስራዎች ዉግንናቸዉ ለህዝብ በመሆኑ፣ ወንድማማችነትንና ትብብርን በማጎለብት ሃገራዊ አንድነት ማረጋገጥን እንደ አንድ ግብ የያዙ ናቸዉ ብለዋል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ በስልጠናው መክፈቻ ላይ አቶ አሽኔ አስቲን የብልፅግና ፓርቲ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ፣ ዶ/ር ጋትሉዋክ ሮ የጋምቤላ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር፣ ከክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላትና አመራሮች፥ ሌሎችም የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።
ሃገራዊ ለዉጡ እዉን ሆኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በተጀመረባቸዉ ያለፉት ሰባት አመታት የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ስብራት ሆኖ የቆየዉን የጋራ ትርክት በመገንባት በመረጃና ማስረጃ ላይ በመመስረት ድህረ እዉነት ዘመን የፈጠራቸዉን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመታገል የሚያስችለንን መሰረት ለመጣል እንዳስቻሉን የተገለፀ ሲሆን፤ ፓርቲያችን የሚከተለዉ አዲሱ መንገድ የመሰባሰብ፣ የአንድነት፣ የፍቅር፣ አንድነት መንገድ መሆኑና ትርክታችንም መደመር እንደሆነ አፅንኦት ተሰጥቶታል።