Prosperity Party

የ2017 ተጠባቂ አፈፃፀሞች

በያዝነው አመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8.4% የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል፡፡ በዘርፍ ደረጃ ደግሞ ግብርና በ6.1%፣ ኢንዱስትሪ በ12.8%፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0%፣ ኮንስትራክሽን በ12.3%፣ አገልግሎት ደግሞ በ7.1% የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134% ብልጫ አሳይቷል፡፡ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7% ወርዷል፡፡ ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ ከ82%-386% ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻሂ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶች በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party