Prosperity Party

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉን ስናከብር ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያሰብን፤ የታረዙትን እያለበስን፤ የተራቡትን እያበላን፤ የተጠሙትን እያጠጣን ፍጹም ሰብዓዊነትን በተላበሰ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሊሆን ይገባል፡፡

በተለይም የፓርቲያችን አመራር፣ አባላት እና ደጋፊዎች በዓሉ በፓርቲያችን የሰው ተኮርነት እና የሰብዓዊነት መርሆች ደምቆ እንዲከበር እያደረጋችሁ የምትገኙትን እንቅስቃሴ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እየጠየቅኩ በድጋሚ ፍቅር፣ ደስታን እና ሰላምን በጋራ የምንቋደስበት መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

አደም ፋራህ ኢብራሂም

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party