ሚዲያዎች ሕፃናትን በመልካም ምግባር የማነፅ አደራ አለባቸው።
ሚዲያዎች ሕፃናትን በመልካም ምግባር የማነፅ አደራ አለባቸው።
የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት 'ናኦታ' የተሠኘ በኦሮሚኛ የሚዘጋጅ የሕፃናት መጽሔት አስጀምሯል።
የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ.ር) ብልጽግና ፓርቲ የሕፃናትን ጉዳይ ስትራቴጂያዊ ጉዳይ አድርጎ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ሚዲያዎች ሕፃናትን ትኩረት አድርገው እንዲሠሩም መደረጉን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት የጀመረው ናኦታ መጽሔትም ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መረጃ እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል።
የመረጃ መጥለቅለቅ ባለበት ዘመን ለሕፃናት በቋንቋቸው ተገቢን መረጃ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ በመኾኑ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ለሕፃናት እድሜያቸውን እና ዕውቀታቸውን ታሳቢ ያደረገ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ናኦታ መጽሔትን ሥራ አስጀምሯል።
በሕፃናት መጽሔት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሣፍንት ተፈራ በሀገራችን እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ ቢኾንም በሀገሪቱ ያሉ መገናኛ ብዙኀን ሕፃናትን ታሳቢ አድርጎ መሥራት እምብዛም ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅትም ክፍተቱን ለመሙላት ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ናኦታ የተባለ በኦሮሚኛ የሚታተም መጽሔት ማስጀሩን ገልጸዋል። ሚዲያዎችም ሕፃናትን በመልካም የማነፅ አደራ አለብንም ብለዋል። ኢፕድ ባለፈው ዓመት ብላቲናት የተባለ በአማርኛ የሚዘጋጅ የሕፃናት መጽሔትን ማስጀመሩን አስታውሰዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሚዲያው የተረሱ ሕፃናትን ትኩረት አድርገን እየሠራን ነው ብለዋል።