"ጉባኤው በሂደትም፣ በውጤትም ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል"
"ጉባኤው በሂደትም፣ በውጤትም ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል"
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከዚህ ጉባኤ የሚጠበቀው አንድ ቁልፍ ነገር ጉባኤው በሂደትም፣ በውጤትም ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ጉባኤ ታሪክ መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካይ ኖሯቸው የሚደረገው ጉባኤ የብልጽግና ጉባኤ ብቻ ነው ብለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ብቃት ያላቸው አመራሮች ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ እንዲመጡ ማድረግ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸው፤ ጉባኤው በሂደትም፣ በውጤትም ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ጉባኤ ታሪክ መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካይ ኖሯቸው የሚደረገው ጉባኤ የብልጽግና ጉባኤ ብቻ ነው በማለት ገልጸዋል።
በጉባኤው አካታችነት፣ አሳታፊነት ዲሞክራሲያዊ በሆኑ የሀሳብ መንሸራሸሮች ዳብሮ ብቃት ያላቸው አመራሮች ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ እንዲመረጡ አድርጎ፣ አሰራር ቀይሶ እና በተለመደው መንገድ ተደምሮ የወጣ እንደሆነ የሚቀጥለው ምዕራፍ ስኬታማ ከባለፈው ታሪካችን መማርመ፣ መገንዘብ፣ ማስተዋል አንቸገርም ብለዋል።
ሁለተኛው የፓርቲው ጉባኤ መሪ ሀሳብ ‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል የሚካሄደውም ለዚሁ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሀሳብ በቃል ይነገራል፣ መጽሐፍ በሰነድ ይሰነዳል፣ በተግባር ይገለጣል፤ ነገር ግን ይህ ሀሳብ በድግግሞሽ እና በልምምድ ውስጥ ባህል ይሆናል ሲሉ ገልጸው፤ ይህም ‘ከቃል እስከ ባህል’ ማለት ነው ብለዋል።
ባህል ማለት ልማድ፣ እሴት እና ትዕምርት ካለማንም ጎትጓች እና ቀስቃሽ በራስ ፈቃድ የሚከወን ነገር መሆኑንም የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።