Prosperity Party
  • የኢህአዴግ 11ኛው መደበኛ ጉባዔ የፓርቲ ውሕደት እንዲፈጸም በተወሰነው መሰረት ህዳር 11 ቀን 2012 .. የኢሕአዴግ ምክር ቤት(ከህወሓት ውጭ) ውሕደቱንና የብልፅግና  ፕሮግራምና የመተዳደሪያ ደንብ በመፅደቁ፣ የኢህአዴግ ማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ይባል የነበረው ከግንባሩ ጋር ከስሞ፤ በብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 15(2)(ረ) መሰረት የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ተብሎ ሲመሰረት ኋላም መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያው ጉባዔ በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 14(2)(ሰ) መሰረት ስያሜው ተሻሽሎ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን እንዲሁም ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በፓርቲው ሁለተኛ ጉባዔ በጸደቀው የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 16(2) (ሰ) መሰረት ስያሜው እንደገና የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተብሎ ከተቋቋሙ የፓርቲ ተቋማዊ መዋቅሮች አንዱ ሆኖ የተመሰረተ ነው፡፡
  • በተሻሻለው የመተዳደሪያ ደንብ አንቀ 25(5) (ሀ) መሰረት ኮሚሽኑ በየደረጃው በሚገኙ የፓርቲ አደረጃጀት ጽሕፈት ቤቶች ያደራጃል፣ የራሱን መዋቅር ይዘረጋል፤ የክልልን እና የአካባቢ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን አባላት በየደረጃው በሚካሄዱ ኮንፈረንሶች ይመረጣሉ። ኮንፈረንስ እስከሚካሄድ ባለው ጊዜ የኮሚሽኑ አባላት መጓደል ወይም አዲስ ማቋቋም ሲያጋጥም ኮሚሽኑ ከየደረጃው ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ጊዜያዊ ምደባ ይሰጣል፣ በሚል በተደነገገው መሰረት የተመሰረተ የፓርቲው ተቋም ነው።
Prosperity Party