የማኅበራዊ ሚዲያ የፈጠረውን መልካም እድል ለሕዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነትን ለማጎልበት አቅም አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያ የፈጠረውን መልካም እድል ለሕዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነትን ለማጎልበት አቅም አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ለሶማሌ ክልል አመራሮች እና ለሚዲያ፣ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ቀጥሏል።
በድህረ እውነት ዘመን የሚነዙ አፍራሽ ሃሳቦችን ለመከላከል የሳይበር ሚዲያውን መልከ ብዙ ስሪት በመረዳት የአገራችንን መልካም ገጽታ እንዲሁም የሕዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነትን ለማጎልበት መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ ነው።
ዘመኑን የዋጀ እና የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ የኮሚኒኬሽን ስልት መጠቀም እንደሚገባም በስልጠናው ተመላክቷል።
የኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የሚዲያ ክትትልን መሠረት ያደረገ አጀንዳ መቅረፅ የሚያስችል ስልጠና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዶትስትሪም መልቲሚዲያ ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር ግርማ ሰጥተዋል።
ስልጠናው በቀጣይ በሌሎች የአገራችን አካባቢዎች የሚሰጥ ይሆናል።