Prosperity Party

የብልጽግና ፓርቲ አመሰራረት


ብልፅግና ፓርቲ  ሶስት የቀድሞ የኢህአዴግ አባል ታርቲዎች የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)፤ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) እንዲሁም አፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አፍዴፓ) ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ቤጉህዴፓ) ፤ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) ፤ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህዴን) እና የሀረሪ ብሔራዊ  ሊግ (ሀብሊ) በመካተት ህዳር 2012 ዓ.ም ተመሰረተ።

በሀዋሳው የኢህአዴግ 11ኛ መደበኛ ጉባዔ የፓርቲ ውሕደት በመዘግየቱ በፍጥነት እንዲጠና ተወሰነ

  • ህዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢሕአዴግ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ ውሕደቱን በ27 አብላጫና በ6 የተቃውሞ ድምፅ አጸደቀ

  • ህዳር 7 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በውህድ ፓርቲው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ ተወያይቶ ረቂቁን ለኢህአዴግ ም/ቤት መራ

  • ህዳር 9 የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ “ብልፅግና ፓርቲ” የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ ከስምምነት ላይ ደረሰ

  • ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢሕአዴግ ምክር ቤት (ከህወሓት ውጭ) ውሕደቱን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

  • ህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የአዲሱን ፓርቲ የወደፊት አቅጣጫ ያመለከተ መግለጫ ወጣ

  • ከዚህ በኋላ እህትና አጋር ድርጅቶች (ከህወሓት ውጭ) ተራ በተራ የብልጽግና ፓርቲን መዋሀዳቸውን ይፋ አደረጉ

  • ህዳር 14 የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል ወሰነ

  • ህዳር 15 የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋ.ህ.አ.ዴ.ን) ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የተጀመረውን ውህደት በመደገፍ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

  • ህዳር 16 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ቤጉህዴፓ እና የሶዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ወሰኑ፡፡

  • ህዳር 17 አዴፓ እና ኦዲፒ ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባዔ ብልፅግናን ለመቀላቀል በሙሉ ድምፅ መወሰናቸው ተነገረ፡፡ የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሃብሊ) በ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔው ብልፅግናን መቀላቀሉ በይፋ አስታወቀ

  • ህዳር 18 ደኢህዴን ብልፅግናን ለመቀላቀል ወሰነ፡፡ በዚሁ ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር) ውህደቱ ህግና ስርዓትን ጠብቆ መፈፀሙን አስታወቁ ፡፡

  • ህዳር 20 ውህድ ፓርቲውን የተቀላቀሉ ፓርቲዎች ፅ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ተካሄደ፡፡

  • ህዳር 21 የብልፅግና ፓርቲን የተቀላቀሉ ድርጅቶች ይፋዊ የስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ አካሄዱ (ብልጽግና ፓርቲ በይፋ ተመሰረተ)፡፡

  • ህዳር 24 ብልጽግና ፓርቲ ህጋዊ እውቅና እንዲሰጠው ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡ ከዚያ ወዲህ ከፍተኛ አመራሮቹ በፓርቲው ፕሮግራሞች ዙሪያ መወያየት ጀምረዋል፡፡

የፓርቲውን የስራ ቋንቋ በተመለከተም አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ፣ ትግርኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች ለስራ ቋንቋነት የተመረጡ ሲሆን፣ ፓርቲው በአገሪቱ ለሚገኙ ቋንቋዎች በሙሉ እውቅና መስጠቱም ተገልጿል፡፡

Prosperity Party