የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት መልዕክት
‘’ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ፣ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ፣ የተዋደደና የተዋኸደ ነው! አማራው በካራማራ ለሀገሩ ሉዓላዊነት ተሰውቶ የካራማራ አፈር ሆኖ ቀርቷል፡፤ትግራዋይ በመተማ ከሀገሬ በፊት አንገቴን ውሰዱ ብሎ የመተማ አፈር ሆኗል፡፡ ኦሮሞው በአድዋ ተራሮች ላይ ስለሀገሩ ደረቱን ሰጥቶ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከአድዋ አፈር ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ሱማሌው፣ ሲዳማው፣ ቤንሻንጉል፣ ወላይታ፣ ጋምቤላው፣ጉራጌው፤አፋሩ፣ ስልጤው፣ ከንባታው፣ ሓዲያው እና ሌሎቹም የኢትዮጲያ ህዝቦች ሁሉ በባድመ ከሀገሬ በፊት እኔን ብለው እንደወደቁ ከባድመ አፈር ጋር ተዋኽደዋል፡፡ አንድ ኢትዮጲያዊ አባት እንዳሉት፣ እኛ ስንኖር ሰዎች፣ ስናርፍ አፈር፤ ስናልፍ ሀገር እንሆናለን፡፡ የየትኛውንም ኢትዮጲያዊ ክቡር ሥጋና ደም በየትኛውም የኢትዮጲያ ክፍል ውስጥ አፈር ሆኖ ታገኙታለችሁ፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ስንኖር ኢትዮጲያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጲያ እንሆናለን፡፡’’ -ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር)