Prosperity Party

በፓርቲው በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 25(6) መሰረት ለኮሚሽኑ የተሰጡት ተግባራት እና ኃላፊነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ) ኮሚሽኑ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤

ለ) የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት እና የሥነ-ምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤

ሐ) የፓርቲው ገንዘብ፣ ንብረትና ሰነዶች በአግባቡ መጠበቃቸውን ቁጥጥር ያደርጋል፤ የፓርቲው አባላት መዋጮ በወቅቱና በትክክል መሰብሰቡን ይቆጣጠራል፤

መ) የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶች እና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል፤

ሠ) ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፤ ይመረምራል፤ የእርምት የውሳኔ ሐሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደአግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል፤

ረ) በኮሚሽኑ የሚቀርበውን የእርምት ሐሳብ የሥራ አስፈጻሚው ካልተቀበለው ለብልፅግና ምክር ቤት ይቀርባል፤ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ እስከ ጉባኤ ድረስ ተፈጻሚ ይሆናል። እንዲሁም በየደረጃው በሚገኙ የኮሚሽን መዋቅር ለፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ የሚቀርበው የእርምት ሐሳብ ተቀባይነት ካላገኘ ኮሚሽኑ አንድ እርከን ከፍ ብሎ ላለው የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ የዲሲፕሊን ክስ ያቀርባል፡፡

ሰ) ዝርዝር የፓርቲ የዲሲፕሊን፣ የኢንስፔክሽንና ቁጥጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለብልፅግና ምክር ቤት አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተል፤

ሸ) የፓርቲው አባላትና አካላት የፓርቲውን ሥነ-ምግባር ማክበራቸውን ይከታተላል፣ የፓርቲ አባላትና አመራር ሊራቸው የገባ የፓቲ ሥነ-ግባከፓርቲ /ቤቶግንቤ ይሰጣ፡፡

ቀ) ሙስናና ብልሹ አሠራር ላይ በፓርቲው ውስጥ ትግል ስለመደረጉ ይከታተላል፣ ያስተባብራልስና ፋቶሲፈጸሙ ተገቢን የእምት ርምእንድ ለሚመለከተው የፓርቲ አካላያቀርል፣ አፈጻጸን ይከተላል፡፡

በ) ሙስና ብሹ አሰራች ዙያ ጥናችን ደርጋል፣ ግንዛቤ ይሰጣል፤

ተ) በየደረጃው የሥነ-ምግባር ጥሰቶችን ይመረምራል፣ ተገቢውን የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤

ነ) ከፓርቲው የፖለቲካ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልዕኮ መሠረት አስፈላጊ ሆነው የተገኙ የምርመራ፣ የክትትል እና የቁጥጥር ሥራዎችን ይሠራል፤

ኘ) በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም ፓርቲውን የሚመለከቱና መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ፤ እንዲሁም በፓርቲው ብልፅግና ምክር ቤት ወይም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኩል ጥያቄ ሲቀርብለት እንደ አንድ ነጻ አጣሪ አካል ሆኖ ያገለግላል፤ የራሱን የውሳኔ ሀሳብ ያካተተ ሪፖርትም ለብልፅግና ምክር ቤት ወይም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀርባል፤

አ) ኮሚሽኑ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንቡ የተሰጡትን ተግባራትና ኃላፊነቶች አስመልክቶ በየወቅቱ ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፡፡ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ-ሐሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤

ከ) ኮሚሽኑ ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለብልፅግና ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል፣ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽን መዋቅር ለሥራ የሚያስፈልግ በጀት ትይዩ ለሚገኙ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ያቀርባሉ፣ ሲጸድቅ ያስተዳድራሉ፤

ወ) ለፓርቲው ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብና ለኮሚሽኑ መመሪያ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽን አባላትን በሁለት ሶስተኛ ድምፅ ያግዳል፤

ዘ) ስለሥራው አፈጻጸም በፌደራል ደረጃ ለፓርቲው ጉባኤ፣ እንዲሁም እንደአግባብነቱ በክልል እና አካባቢያዊ መዋቅሮች አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ላለው ኮሚሽን እና ለኮንስ ሪፖርት ያቀርባሉ፤

ዠ) ይህንን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በማድረግ የኮሚሽኑን የውስጥ አሠራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል።

Prosperity Party