Prosperity Party

መረጃ ማጣራትና የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን ክህሎት ማሳደግ የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት ለመምራት ወሳኝነት አለው!

ያልተጣሩ፣ ምንጫቸው ያልታወቁና የሀገርንና የህዝብን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎች በስፋትና በፍጥነት የሚሰራጭበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

ስለሆነም ዘመኑን የዋጀና መረጃዎችን ማጥራትና ቀውስን መቆጣጠር የሚያስችል የተግባቦት እውቀትና ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል።

በብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት መምራት የሚያስችል ግንዛቤ የሚፈጥር ስልጠና ለፓርቲው የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት አመራሮች እና ባለሞያዎች በአዲስ አበባ መስጠት ጀምሯል።

በዕለቱ መርሀ ግብር የከሰዓት ውሎም "መረጃ ማጣራትና የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን" ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል።

የኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት መረጃን ማጣራትና የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ስልጠና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዳታ ማሰባሰብ እና ማጠናቀር ዲቪዥን ሃላፊ አቶ ደሳለኝ አዱኛ ሰጥተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አንቂዎች "የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት" በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ነው።

ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ይሆናል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party