Prosperity Party

የሌማት ትሩፋት የልማት ዘመቻችን ግቦች 

★ ስጋ ፣እንቁላል፣ማር እና ወተት የቅንጦት ሳይሆን በቀላሉ የሚገኙ አማራጮች እንዲሆኑ ማድረግ። 

በሀገራችን እነኚህ ምርቶች በቅንጦት ደረጃ የሚፈረጁ ምርቶች እንጂ እለት በእለት በምግብ አማራጮቻችን ውስጥ የሚገኙ ግብአቶች አይደሉም።ይህም ሊሆን የቻለው ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት እምብዛም አመርቂ ባለመሆኑ የተነሳ ነው።በመሆኑም ይህን ችግር በተረባረበ አቅም እና በቴክኖሎጂ በታገዘ አካሄድ  በመፍታት ዘርፈ ብዙ አማራጮችን መፍጠር እንችላለን።በቀላሉም ወተት፣ማር፣ስጋ እና እንቁላል በገበያው እንዲገኙ ማድረግ እንችላለን።

★ ሀገራችን በእንስሳት ተዋእፆ ያላትን እምርታ ማሳደግ:: 

በእንሰሳት ተዋእፆ ምርቶች ላይ የተወሰነ ስራ ቢሰራ ፍሬ ሊያፈራ የሚችል ሀብት በሀገራችን ውስጥ አለ።ለከብቶች የሚስማማ አየር፣ለንቦች አመቺ የሆነ ስነ ምህዳር፣ስጋ እና እንቁላል ሊያትረፈርፍ የሚችል ተፈጥሮ አለን።ይህን በከፍተኛ ንቅናቄ  አውጥተን በመጠቀም እንደ ሀገር ያለንን እምርታ ማሳደግ እንችላለን። 

★ ተመጣጣኝ ምግብ በብዛት እና በጥራት በገበያው እንዲኖር ማስቻል። 

ምርት ሲበዛ በግብአቶች ላይ የሚኖረው የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ይመጣል።በመሆኑም ስጋ፣እንቁላል ማር እና ወተት በብዛት በማምረት ወደ ገበያው የሚቀርበውን የምግብ አማራጭ በማስፋት በምግቦች ላይ የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጠር  እንዲሁም የተመጣጠነ የምግብ ስርአት የዳበረ የአመጋገብ ዘይቤ መገንባት እንችላለን!! 

★ የምግብ አማራጮቻችንን ሰፊ በማድረግ የአመጋገብ ባህላችንን ማሻሻል። 

ምግብ ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው!!የምግብ አማራጮቻችን በሰፉ ቁጥር የአመጋገብ ባህላችንም እንደሚሻሻልም እውን ነው።በተለይም እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ላይ እና ለውስጥ ፍላጎታችን መጠቀም ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት የአመጋገብ ባህላችንን ማሻሻል የሌማት ትሩፋት ዘመቻችን ሌላኛው ግብ ነው። 

★ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የምግብ ስርአት መዘርጋት። 

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወተት፣ማር፣እንቁላል እና ስጋ በቀላሉ ሊያገኘው የሚገባ የምግብ አማራጭ መሆን እንዳለበት ፓርቲያችን በፅኑ ያምናል።ሌሎች የምግብ አማራጮች ተደራሽ በሆኑበት ልክ እነኚህም ምርቶች በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።ለዚህም እልፍ አእላፍ የሆነውን በሀገራችን ውስጥ ያለውን ሀብት በቴክኖሎጂ በማዳበር ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የሆነ የምግብ ስርአት መዘርጋት ይኖርብናል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party