የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት 2017 ዓ.ም በጀት አመት ያለፉት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት 2017 ዓ.ም በጀት አመት ያለፉት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።
የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና ሌሎች የዋና ፅ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ነው የፓርቲው ያለፉት ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ የተደረገው።
በዚሁ ወቅት ክቡር አቶ አደም ፋራህ እንደገለፁት ባለፋት አመታት በተሰሩ ውጤታማ ስራዎች የፓርቲው ንቅናቄ የመፍጠርና የማስፈፀም አቅም ማደጉን አንስተዋል።
ፓርቲው ሀገራዊ ፓርቲ እንደመሆኑ ከላይ እስከ ታች የሚናበብ፣ ስራዎችን አቀናጅቶ መምራት የሚችል፣ ለህዝብ የተገባውን ቃል መፈፀም፣ በአመራር ደረጃ ተቀራርቦ መስራት፣ የፓርቲ ዲፕሎማሲ እንዲሁም ከፓለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራት በዋናነት የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን አብራርተዋልመ
በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት በተካሄደው የሪፖርት ግምገማ መርሐ ግብር እንደተመለከተው የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ባለፉት ወራት በተለያዩ ዘርፎች ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ አፈጻጸም አስመዝግቧል።
በፖለቲካና አቅም ግንባታ፣በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ፣ በአደረጃጀት፣ በህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት፣ በስትራቴጂክ እና ስራ አመራር፣በሀብት አስተዳደር፣በጥናትና ምርምር ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያፋጠኑ የትርክት የበላይነትንም ያስገኙ መሆናቸው ከመድረኩ ተጠቅሷል።
የፓርቲው አምስተኛ አመት የምስረታ በዓል ፣ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ፣ መጋቢት 24 መርሐ ግብሮች የፓርቲውን ስኬቶች ባጎላ መንገድ መከናወናቸው የፓርቲው አፈፃፀም ውጤታማነት ማሳያ መሆናቸው ተብራርቷል።
የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም የሀገርና የህዝብን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ አመራሩና አባላቱ በተቀናጀና ወጥነት ባለው መንገድ መስራት እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ አሳስበዋል።